የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ  ኢብራሒም ሙሀመድ (ዶ.ር)

የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2022 ዓ.ም በህግና በገበያ ስርዓት የሚመራ ዘመናዊና ተወዳዳሪ የንግድና ግብይት ስርዓት ተፈጥሮ ማየት የሚል ራዕይ ነድፎ ራዕዩን ለማሳካት ሌት ተቀን እየሰራ ያለ ተቋም ነዉ፡፡ ተቋሙ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪ፣ ፍትሀዊና ተደራሽ የንግድና ግብይት ስርዓት ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል። የንግድ ስርአቱን የሚያዛቡ አሻጥሮችን፣ የደላላ ጣልቃ ገብነትን፣ የገበያ ተደራሽነት ችግሮችን፣ ህገወጥ የኬላ ቀረጦችን እና የምርትጥራት ችግሮችን ለመፍታትዘርፈ ብዙ ተግባራትን ከማከናወንም በላይ ንግድ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የታገዘ እንዲሆን አዳዲስ ሲስተሞችን የማስለማትና ሌሎች ንግድና ግብይቱን ወደ ህጋዊ አሰራራ የሚያመጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡  ለህጋዊ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና በህገ ወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው በተገኙ ህገ-ወጦች ላይ ደግሞአስተዳደራዊና ህጋዊ ርምጃ በመዉሰድ የሸማቹን ደህንነት ለማስጠበቅ ጥረት ተደርጓል።   ከንግዱ ጋር ተሳስሮ በልዩ ትኩረት እየተተገበረ ያለው ሌላኛው ዘርፍ የግብይት ልማቱ ዘርፍ ነው። ንግዱ ጤናማና የሸማቹን ደህንነት የሚያስጠብቅ እንዲሆን ነባር የገበያ ማዕከላት እንደተጠበቁ ሆኖ በ2017 በጀት ዓመት በ8 ሪጅዎ ፖሊታን ከተሞች የተጀመሩ አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ የሚያገናኙ ዘመናዊ የ2ኛ ደረጃ የግብይት ማዕከላትን ተጠናቀው ወደስራ እንዲገቡ ከማድረግ ባሻገር ይህንን መልካም ተሞክሮ ለማስፋት በ2018 በጀት ዓመት ደግሞ በ7 የዞን ከተሞች ተጨማሪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ በማስገንባት ላይ እንገኛለን፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም የግብይት ተዋንያንን የግንዛቤ፣ የአሰራር፣ የፋይናንስና የቴክኖሎጅ ችግር በመፍታት ምርት ለሸማቹ እንዲያቀርቡ በማድረግ የኑሮ ዉድነቱ ያደርስ የነበረዉን ተጽእኖ መቀነስ ተችሏል።   የወጭ ንግድን ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫ በማድረግና ግብ በማስቀመጥ በቅርበትመደገፍ በመቻሉካለፉት አመታት ብልጫ ያለዉ የቅባት እህል፣ጥራጥሬ፣ ቡና እንዲሁም የቀንድ ከብት፣ በግና ፍየል ለዉጭ ገበያ በማቅረብ ክልሉ ለዉጭ ምንዛሬ ግኝት የራሱን ትልቅ ድርሻ አበርክቷል።   በመሆኑም የንግድና ግብይት ልማት ለአገር ውስጥና ለውጭ ንግዱመቀላጠፍናለሀገራዊ እድገቱ ያለው ሚናከፍተኛ ስለሆነና ዘርፉ በባህሪው የሁሉንም አካል እርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ አሰራሩ እንዲጠናከርና የታሰበው ግብ እንዲሳካ ሁላችንም የበኩላችን እንወጣ ስል ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡                                         

                             አመሰግናለሁ!

Scroll to Top