በደቡብ ጎንደር ዞን በእብናት ከተማ አስተዳደር በእብናት ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እና በውብእናት የሚዲያና ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ጋር በመተባበር በዛሬ ዕለት የንግድ ኢግዚቪሽንና ባዛር በይፋ ተጀምሯል፤
በንግድ ኢግዚቪሽንና ባዛሩ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእብናት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ አቶ አለበል ጌጤ ይህ ፕሮግራም የተዘጋጀው ዋና አላማው የተቀዛቀዘውን የንግድ እንቅስቃሴ ለማነቃቃትና የሸቀጦችን የዋጋ ንረት ለመቀነስ የታለመ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህ አጋጣሚ የከተማችንና የአካባቢው ማህበረሰብ የሚፈልጉትን የምርት አይነቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆን ሲሉ ተናግረዋል።
ንግድ ኢግዚቪሽንና ባዛር መካሄዱ የዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና በተመጣጣኝ ዋጋ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርታቸዉን በቀጥታ ለተጠቃሚዉ ማህበረሰብ ከማድረስ ባሻግር ምርቱን በአንድ ላይ እንዲሸምቱ በማድረግ ጊዜንም ገንዘብንም ይቆጥባል፤የከተማውን ኢኮኖሚም እንደሚያነቃቃም አቶ አለበል አክለዋል ገልጸዋል።
የእብናት ከተማ ንግድና ገቢያ ልማት ጽ/ቤት ኋላፊ አቶ ያብባል ሞላ በበኩላቸው እብናት ከተማ ባዛር መከፈቱ ማህበረሰቡ ከአንድ ቦታ ላይ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ከማግኝት በተጨማሪ ቀጥታ ሻጭ ከሸማች ጋር ስለሚገናኝ የዋጋ ንረትን ያረጋጋል፣የአካባቢዉን ኢኮኖሚም ከማነቃቃት ባሻገር፣የስራ ዕድልም እንደሚፈጥር ተናግረው፤ የአካባቢው ማህበረሰብ በባዛሩ ያሉ ምርቶችን በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በዚህ የንግድ ኢግዚቪሽንና ባዛር መርሃ ግብር ላይ የእብናት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ አቶ አለበል ጌጤ፣የእብናት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታርቆ አሰፍ፣የእብናት ከተማ አስተዳደር ንግድና ገቢያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያብባል ሞላና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።
የንግድ ኢግዚቪሽንና ባዛሩም ለቀጣይ ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይም ተገልፃል።
መስከረም 10/2019 ዓ/ም


