በሰሜን ሸዋ ዞን በ2019 በጀት አመት ዓመት ከ576 ሺህ ኩንታል በላይ የማሾ ምርት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

በሰሜን ሸዋ ዞን በ2019 በጀት አመት ዓመት ከ576 ሺህ ኩንታል በላይ የማሾ ምርት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

ከሚመረተዉ ምርትም ከ53 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

​የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዘውገ ንጉሴ እንደገለጹት ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ 108 ሺህ 174 ኩንታል ማሾ ለሀገር ውስጥ ማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ 13 ሚሊዮን 571 ሺህ 750 ዶላር ማግኘት እየተሰራ ነው።

በወረዳው በሄክታር እስከ 25 ኩንታል ማሾ እንደሚመረት የገለጹት የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወሰኔ አንበርብር በተያዘው የመኸር ዘመን ከለማው 142 ሄክታር መሬት 3 ሺህ 550 ኩንታል ምርት ይጠበቃል ብለዋል።

​የደላላና የገበያ ችግሮችን ለመፍታት ላኪዎች ከአምራቾች ጋር በቋሚነት በሚገቡት የውል ሥርዓት መሠረት ግብይቱ እንዲፈጸም ማድረግ የመጀመሪያው መፍትሔ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘውገ ንጉሴ ናቸዉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ገዢዎች ከአርሶ አደሮች ወይም ነጋዴዎች በቀጥታ ገዝተው ወደ ማዕከላዊ ገበያ የሚያስተላልፉበት አሠራር መኖሩን ጠቅሰዋል።

ይህም አርሶ አደሮች በወቅታዊ ዋጋ የመሸጥ መብታቸዉን የሚያስከብርላቸዉና ያለምንም ደላላ ጣልቃ ገብነት ምርታቸዉን በጥራት ወደ ማዕከላዊ ገበያ እንዲገባ የሚያደርግ በመሆኑ መምሪያው አስፈላጊውን ክትትል እንደሚያደርግ አብራርተዋል።

​ከዞኑ ግብርና መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በመኸር ወቅት ከተሸፈነዉ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የማሾ ሰብል ከ361 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ጥቅምት 1872019 ዓ.ሞ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top