ኢብራሒም ሙሐመድ(ዶ/ር)
የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ሠራተኞች እና የሥራ ኀላፊዎች “ኢትዮጵያ የተስፋ ምድር” በሚል መሪ መልዕክት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክተው የፓናል ውይይት በባሕር ዳር ከተማ አካሂደዋል።
“እኛ ዓባይን እንገንባ ብንል አቅም የለንም። የውጭ ወዳጅ ሀገራትንም እርዱን ብንል ግብጽን ላለማስቀየም ፈቃደኛ አይኾኑም ። ቀጣዩ ትውልድ በራሱ ንዋይ ይገነባዋል። ጥናቱ በክብር ይቀመጥ” ሲሉ በ1952 ዓ .ም ይህ ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ ንግግር የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ትንቢታዊ አደራ ዛሬ እነሆ እውን ሆኖ ዳግመዊ አድዋ ተበሰረ፡፡
የያኔው አሻጋሪ መሪ ዕይታቸው እውነትም በዚህ ትውልድ ገቢር ኾነ። ቃል በተግባር ያለምንም መሸራረፍ ተከወነ። ያኔ ቀጣዩ ትውልድ ተብሎ የተነገረላቸው ያሁኑ ትውልድ ቃላቸውን አከበሩ። የማይፋቅ ታሪክንም ሠሩ።
የታሪክ ባለቤት የኾኑት የዚህ ዘመን ትውልድም የሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ ደስታቸውን በተለያዩ መንገዶች እያስተላለፉ ይገኛሉ። ሌሎች ደማቅ ታሪኮችንም ለመስራት እነሆ ርዕይ ሰነቁ ፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት የሥራ ኀላፊዎች እና ሠራተኞች “ኢትዮጵያ የተስፋ ምድር” በሚል መሪ መልዕክት የግድቡን መመረቅ አስመልክተው ዛሬ ውይይት አድርገዋል።
የፓናል ውይይቱን የመሩት የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢብራሒም ሙሐመድ (ዶ.ር) “የራሳችን አቅም መፈተሽ እና መተባበር ከቻልን እንደምንችል አይተናል፤ በዚህም ሁሉም ሊኮራ ይገባል” ብለዋል። ኢትዮጵያ ከዚህም በላይ ማሳካት እደምትችል የታየበት ፕሮጀክት መኾኑንም ለተወያዮች ገልጸዋል።
ከግጭት አዙሪት መውጣት ከተቻለ እና ትውልዱ ታሪክ መሥራት የማይታክተው ከኾነ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በላይም ታሪክ መጻፍ ይቻላል ነው ያሉት። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ጠላቶች የሀገሪቱን ልማት ሊያስቆሙት እንደማይችሉ የታየበት ምዕራፍ እንደሆነም አስገንዝበዋል።
የባዕዳን ተጽዕኖ እንደተጠበቀ ኾኖ ግድቡ ዳር እንዳይደርስ የውስጥ ባንዳም ተጽዕኖ እንደነበረበት አስታውሰዋል። በቀጣይ ግን ሁሉም ዜጋ ወደ ውስጥ መመልከት እና አንድነትን መርህ ማድረግ ይኖርበታል ነው ያሉት።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ እንደ ትውልድ ምን ትምህርት እንደሚሰጥ ማሰብ ይገባል ነው ያሉት ዶክተር ኢብራሒም። ችግሮችን ሁሉ በመመከት ዳር የደረሰው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአይበገሬነት ማሳያ እንደኾነም ነው ቢሮ ኀላፊው የተናገሩት።የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ሠራተኞች እና የሥራ ኀላፊዎች “ኢትዮጵያ የተስፋ ምድር” በሚል መሪ መልዕክት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክተው የፓናል ውይይት በባሕር ዳር ከተማ አካሂደዋል።
“እኛ ዓባይን እንገንባ ብንል አቅም የለንም። የውጭ ወዳጅ ሀገራትንም እርዱን ብንል ግብጽን ላለማስቀየም ፈቃደኛ አይኾኑም ። ቀጣዩ ትውልድ በራሱ ንዋይ ይገነባዋል። ጥናቱ በክብር ይቀመጥ” ሲሉ በ1952 ዓ .ም ይህ ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ ንግግር የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ትንቢታዊ አደራ ዛሬ እነሆ እውን ሆኖ ዳግመዊ አድዋ ተበሰረ፡፡
የያኔው አሻጋሪ መሪ ዕይታቸው እውነትም በዚህ ትውልድ ገቢር ኾነ። ቃል በተግባር ያለምንም መሸራረፍ ተከወነ። ያኔ ቀጣዩ ትውልድ ተብሎ የተነገረላቸው ያሁኑ ትውልድ ቃላቸውን አከበሩ። የማይፋቅ ታሪክንም ሠሩ።
የታሪክ ባለቤት የኾኑት የዚህ ዘመን ትውልድም የሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ ደስታቸውን በተለያዩ መንገዶች እያስተላለፉ ይገኛሉ። ሌሎች ደማቅ ታሪኮችንም ለመስራት እነሆ ርዕይ ሰነቁ ፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት የሥራ ኀላፊዎች እና ሠራተኞች “ኢትዮጵያ የተስፋ ምድር” በሚል መሪ መልዕክት የግድቡን መመረቅ አስመልክተው ዛሬ ውይይት አድርገዋል።
የፓናል ውይይቱን የመሩት የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢብራሒም ሙሐመድ (ዶ.ር) “የራሳችን አቅም መፈተሽ እና መተባበር ከቻልን እንደምንችል አይተናል፤ በዚህም ሁሉም ሊኮራ ይገባል” ብለዋል። ኢትዮጵያ ከዚህም በላይ ማሳካት እደምትችል የታየበት ፕሮጀክት መኾኑንም ለተወያዮች ገልጸዋል።
ከግጭት አዙሪት መውጣት ከተቻለ እና ትውልዱ ታሪክ መሥራት የማይታክተው ከኾነ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በላይም ታሪክ መጻፍ ይቻላል ነው ያሉት። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ጠላቶች የሀገሪቱን ልማት ሊያስቆሙት እንደማይችሉ የታየበት ምዕራፍ እንደሆነም አስገንዝበዋል።
የባዕዳን ተጽዕኖ እንደተጠበቀ ኾኖ ግድቡ ዳር እንዳይደርስ የውስጥ ባንዳም ተጽዕኖ እንደነበረበት አስታውሰዋል። በቀጣይ ግን ሁሉም ዜጋ ወደ ውስጥ መመልከት እና አንድነትን መርህ ማድረግ ይኖርበታል ነው ያሉት።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ እንደ ትውልድ ምን ትምህርት እንደሚሰጥ ማሰብ ይገባል ነው ያሉት ዶክተር ኢብራሒም። ችግሮችን ሁሉ በመመከት ዳር የደረሰው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአይበገሬነት ማሳያ እንደኾነም ነው ቢሮ ኀላፊው የተናገሩት።
በቀጣይ ሀገሪቱ ለምታስባቸው ፕሮጀክቶች ከግድቡ ትምህርት መውሰድ መሠረታዊ ነገር ነው ሲሉም አክለዋል።
“ኢትዮጵያ የተስፋ ምድር” በሚል ርዕስ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የቢሮው የግብይት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ወ/ሮ አትክልት አሳቤ ግድቡ የመላው ኢትዮጵያውያን የላብ ውጤት እንደኾነ በሰነዱ ላይ አመላክተዋል። ቁጥር ሁለት ዓድዋ የተደገመበት ታሪካዊ ስኬት ነው ሲሉም አትተዋል።
ግድቡ የበሳል መሪዎች የመወሰን ብቃት ታይቶበታል ነው ያሉት። የዲፕሎማሲ ጥበብም በተግባር የታጀበበት ስኬት እንደኾነ ነው የገለጹት ምክትል ኀላፊዋ። የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የፋይናንስ ምንጭ ሕዝብ እና መንግሥት እንደሆነ ለህዝብ በማብሰርም የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ መጋቢት 24/2003 ዓ.ም የመሰረት ድንጋዩን እንዳስቀመጡ በማውሳት ለዚህ ስራቸው ዋጋ ሰጥጠዋል፡፡ የሕዳሴ ግድቡ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የተስፋ ፈር የቀደደ እንደኾነ በተወያዮች ተነስቷል። በስኬቱም ከልብ እንደተደሰቱ በመድረኩ ተወያዮች በሰፊው ተገልጿል።
የዓባይ ጉዳይ የንግግር ብቻ ሳሆን በተግባርም ተተርጉሟል ነው ያሉት። ግድቡን ከዚህ ላደረሱ ሁሉ ምሥጋና እንደሚገባቸውም ተወያዮች በአጽንኦት አንስተዋል።
“በወንድማማችነት መንፈስ ነጋችን አብረን እናቅና!!!“