የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ፡፡
“ብሔራዊ ጥቅምና ጂኦ- ስትራቴጂ ቁመና” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ በተዘጋጀ ሰነድ የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት አካሂደዋል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ የማንሰራራት ላይ የምትገኝ ለቀጠናው ሰላም እና እድገት ጉልህ ድርሻ ያላት የታላቅ ህዝቦች መኖሪያ ናት ሲሉ የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፈንታው ፈጠነ መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ሲከፍቱ ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያን የመለወጥ ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው፡፡ ሁሉም ይመለከተዋል፡፡ ሀገሪቱ እያደረገች ያለውን የመለውጥና ብልፅጋናን የማረጋገጥ ተግባር በባለቤትነት መደገፍ ይገባል ሲሉ ምክትል ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና(ራስነን መቻል፣ከድህነት መውጣት፣መበልጸግ) ፣ ሀገራዊ ህልውና እና ደህንነት ማስፈን፣ ፖለቲካዊ አቅምንና ተጽዕኖ ፈጣሪነትን ማሳደግ፣ የባህል ነፃነትናተፅኖ ፈጣሪነት ማጉላት፣የህዝቦች ማህበራዊ ልማት(ትምህርት፣ጤና፣ማህበራዊ ዋስትና)…. የመሳሰሉ የብሔራዊ ጥቅም መሰረታዊ ግቦቻችን መሳካት ሁሉም የየድራሻውን መወጣት ይኖርበታል ሲሉ የመወያያ ፅሁፉን ያቀረቡት የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አማካሪ ሙሀመድ ጀማል(ዶ/ር) አስገንዝበዋል፡፡
ብሔራዊ ጥቅም የሀገራዊ ህልውና፣ ደህንነትና ብልፅግና ጉዳይ ነው፡፡ ጂኦ- ስትራቴጂክ ቁመና አጀንዳችን የሀገር የህዝብና የትውልድ አጀንዳ ነው ስለሆነም በብሄራዊ ጥቅማችን ላይ ሁላችንም አንድ መሆን ይገባል ሲሉ አማካሪው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም ለብሄራዊ ጥቅማችን መጠበቅ ሁሉም የተጣለበትን ኃላፊነት በቁርጠኝነት በቅንነት መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በኢኮኖሚ የበላይነትን ማረጋገጥ ከተቻለ የትኛውንም የሀገር ጥቅም ማስጠበቅ የሚቻል መሆኑን የአለም ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳይ ነው – በመሆኑም አንዳችን በሌላኛው ለይ እጣት መቀሳሰርን ትተን የጀመርነውን ሀገራዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ከታች እሰከ ላይ ያለ ማንኛውም አካል በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ሲሉ የውይይት መድረኩን የመሩት የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አቢታ ገበያው አሳስበዋል፡፡
