













የገበያ ማዕከላት መስፋፋት የዋጋ ንረትን ለመቀነስና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት ወሳኝ መፍትሔ ሆነዋል-ሸማቾች
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሀይቅ ከተማ የመስክና የቢሮ ስራዎችን ምልከታ አደረገ።
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሀይቅ ከተማ የመስክና የቢሮ ስራዎችን ምልከታ አደረገ።
"ህጋዊ፣ ተደራሽና ዘመናዊ የንግድና የግብይት ስርዓት እንገነባለን" በሚል መሪ መልዕክት፣ የንግድ ቀን በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በጫጫ ክፍለ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት በድምቀት ተከብሯል።
photo_2026-06-17_09-59-39 (6)
photo_2026-06-17_09-59-39
photo_2026-06-17_09-59-40 (2)
photo_2026-06-17_09-59-40 (3)
photo_2026-06-17_09-59-40 (4)
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሀይቅ ከተማ የመስክና የቢሮ ስራዎችን ምልከታ አደረገ።
photo_2026-06-17_09-59-40 (6)
photo_2026-06-17_09-59-40 (7)
photo_2026-06-17_09-59-40 (8)
photo_2026-06-17_09-59-40














የቢሮ ኃላፊ መልዕክት

ኢብራሒም ሙሀመድ (ዶ.ር)
የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ
የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2022 ዓ.ም በህግና በገበያ ስርዓት የሚመራ ዘመናዊና ተወዳዳሪ የንግድና ግብይት ስርዓት ተፈጥሮ ማየት የሚል ራዕይ ነድፎ ራዕዩን ለማሳካት ሌት ተቀን እየሰራ ያለ ተቋም ነዉ፡፡ ተቋሙ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪ፣ ፍትሀዊና ተደራሽ የንግድና ግብይት ስርዓት ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል። የንግድ ስርአቱን የሚያዛቡ አሻጥሮችን፣ የደላላ ጣልቃ ገብነትን፣ የገበያ ተደራሽነት ችግሮችን፣ ህገወጥ የኬላ ቀረጦችን እና የምርትጥራት ችግሮችን ለመፍታትዘርፈ ብዙ ተግባራትን ከማከናወንም በላይ ንግድ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የታገዘ እንዲሆን አዳዲስ ሲስተሞችን የማስለማትና ሌሎች ንግድና ግብይቱን ወደ ህጋዊ አሰራራ የሚያመጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ለህጋዊ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና በህገ ወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው በተገኙ ህገ-ወጦች ላይ ደግሞአስተዳደራዊና ህጋዊ ርምጃ በመዉሰድ የሸማቹን ደህንነት ለማስጠበቅ ጥረት ተደርጓል።
News | ዜናዎች
June 8, 2026
Comment (0)
ኢብራሒም ሙሐመድ(ዶ/ር) የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ሠራተኞች እና የሥራ ኀላፊዎች “ኢትዮጵያ የተስፋ ምድር” በሚል መሪ መልዕክት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክተው የፓናል ውይይት በባሕር ዳር ከተማ አካሂደዋል። “እኛ ዓባይን እንገንባ ብንል አቅም የለንም። የውጭ ወዳጅ ሀገራትንም እርዱን ብንል ግብጽን ላለማስቀየም ፈቃደኛ አይኾኑም ። ቀጣዩ ትውልድ በራሱ ንዋይ ይገነባዋል። ጥናቱ በክብር ይቀመጥ” ሲሉ በ1952 ዓ .ም ይህ ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ ንግግር የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ትንቢታዊ አደራ ዛሬ እነሆ እውን ሆኖ ዳግመዊ አድዋ ተበሰረ፡፡ የያኔው አሻጋሪ መሪ ዕይታቸው እውነትም በዚህ ትውልድ ገቢር ኾነ። ቃል በተግባር ያለምንም መሸራረፍ ተከወነ። ያኔ ቀጣዩ ትውልድ ተብሎ የተነገረላቸው ያሁኑ ትውልድ ቃላቸውን አከበሩ። የማይፋቅ ታሪክንም ሠሩ። የታሪክ ባለቤት የኾኑት የዚህ ዘመን ትውልድም የሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ ደስታቸውን በተለያዩ መንገዶች እያስተላለፉ ይገኛሉ። ሌሎች ደማቅ ታሪኮችንም ለመስራት እነሆ ርዕይ ሰነቁ ፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት የሥራ ኀላፊዎች እና ሠራተኞች “ኢትዮጵያ የተስፋ ምድር” በሚል መሪ መልዕክት የግድቡን መመረቅ አስመልክተው ዛሬ ውይይት አድርገዋል።...
