













የገበያ ማዕከላት መስፋፋት የዋጋ ንረትን ለመቀነስና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት ወሳኝ መፍትሔ ሆነዋል-ሸማቾች
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሀይቅ ከተማ የመስክና የቢሮ ስራዎችን ምልከታ አደረገ።
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሀይቅ ከተማ የመስክና የቢሮ ስራዎችን ምልከታ አደረገ።
"ህጋዊ፣ ተደራሽና ዘመናዊ የንግድና የግብይት ስርዓት እንገነባለን" በሚል መሪ መልዕክት፣ የንግድ ቀን በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በጫጫ ክፍለ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት በድምቀት ተከብሯል።
photo_2026-06-17_09-59-39 (6)
photo_2026-06-17_09-59-39
photo_2026-06-17_09-59-40 (2)
photo_2026-06-17_09-59-40 (3)
photo_2026-06-17_09-59-40 (4)
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሀይቅ ከተማ የመስክና የቢሮ ስራዎችን ምልከታ አደረገ።
photo_2026-06-17_09-59-40 (6)
photo_2026-06-17_09-59-40 (7)
photo_2026-06-17_09-59-40 (8)
photo_2026-06-17_09-59-40














የቢሮ ኃላፊ መልዕክት

ኢብራሒም ሙሀመድ (ዶ.ር)
የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ
የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2022 ዓ.ም በህግና በገበያ ስርዓት የሚመራ ዘመናዊና ተወዳዳሪ የንግድና ግብይት ስርዓት ተፈጥሮ ማየት የሚል ራዕይ ነድፎ ራዕዩን ለማሳካት ሌት ተቀን እየሰራ ያለ ተቋም ነዉ፡፡ ተቋሙ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪ፣ ፍትሀዊና ተደራሽ የንግድና ግብይት ስርዓት ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል። የንግድ ስርአቱን የሚያዛቡ አሻጥሮችን፣ የደላላ ጣልቃ ገብነትን፣ የገበያ ተደራሽነት ችግሮችን፣ ህገወጥ የኬላ ቀረጦችን እና የምርትጥራት ችግሮችን ለመፍታትዘርፈ ብዙ ተግባራትን ከማከናወንም በላይ ንግድ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የታገዘ እንዲሆን አዳዲስ ሲስተሞችን የማስለማትና ሌሎች ንግድና ግብይቱን ወደ ህጋዊ አሰራራ የሚያመጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ለህጋዊ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና በህገ ወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው በተገኙ ህገ-ወጦች ላይ ደግሞአስተዳደራዊና ህጋዊ ርምጃ በመዉሰድ የሸማቹን ደህንነት ለማስጠበቅ ጥረት ተደርጓል።
News | ዜናዎች
June 12, 2026
Comment (0)
በባህር ዳር ከተማ የተገነባው ሁለተኛ ደረጃ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ። * * * * * * የገበያ ማዕከላትን በማስፋፋትና ምቹ የምርት ትስስር በመፍጠር ዘመናዊ ግብይትን እውን ለማድረግ እንተጋለን- በሚል መሪ ሀሳብ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በተገኙበት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። የገበያ ማዕከሉ በፌደራል መንግስት በተቀመጠው አቅጣጫ በክልላች መንግስት ፈፃሚነት የህብረተሰባችንን የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃለል ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዲኖረው ታስቦ መገንባቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የተከበሩ አቶ አረጋ ከበደ ማዕከሉን መርቀው ሲከፍቱ ገልፀዋል።...
June 8, 2026
Comment (0)
የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸሙ በመገምገም በ2018 በጀት ዓመት ዕቅዱ ላይ ከዞንና ከተማ አስተዳዳር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል። የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢብራሂም ሙሐመድ (ዶ/ር) ተቋማቸው በ2017 በጀት ዓመት የንግድ ሥርዓቱን በማሳለጥ ሕዝቡን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ መሥራቱን ገልጸው በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት ይገባል ብለዋል። በፌዴራል ደረጃ በተደረገ የ2017 አፈጻጸም ውድድርም ተቋማቸው በሁለት ዘርፎች በአገር አቀፍ ደረጃ የሁለተኛ ደረጃ ተሸላሚ መሆኑን አውስተዋል። የጥራጥሬ እና ቅባት እህል ኤክስፖርት ላይም የተሸለሙ ባለሃብቶች መኖራቸውን ጠቅሰው ለውጤቱ የቢሮው የተዋረድ ተቋማት ድጋፍ እና ጥረት ከፍ ያለ መሆኑን በማንሳት አመስግነዋል።...
June 8, 2026
Comment (0)
በወቅታዊ የነዳጅ ስርጭት ችግሮች ዙሪያ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከሚመለከታቸወ አካላት በተገኙበት ውይይት አካሒዳል። ለመወያያ መነሻ የሚሆን ጽሁፍ በንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ በአቶ ፈንታው ፈጠነ ቀርቧል። በነዳጅ አጠቃቀም ዙሪያ የወጡ አዋጆችን ፣ በአዋጁ መሰረት የተሰሩ ስራዎችን፣ በአሰራር ላይ የመስተዋሉ ተግዳሮቶችንና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በዝርዝር ለታዳሚያን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ፈንታው ፈጠነ አቅርበዋል ። በፀጥታና በፈፃሚ ስም እየገቡ የነዳጅ ስርጭት ሂደቱን የሚያውኩ አካላት እንዳሉም አቶ ፈንታው ሳይጠቁሙ አላለፋም። ተሳታፊ አካላት በአሰራሩ ላይ እያጋጠሙ የሉ ችግሮችንና መፍትሔዎችን በዝርዝር አንስተዋል። ከተሰጡ አስተያየቶ አንድ የፖሊስ አመራር እንደገለፁት ነዳጅ ማደያ ተቋማዊ ሳይሆን ግለሰባዊ ነው ። አስተያየት ሰጭው ነዳጅ ማደያ ላይ ደላላው ፣ ማደያውና አንድ ሌላ ተጠቃሚ አለ ያሉ ሲሆን ለወረፋ አስከባሪ በቀን 5000 ብር የሚከፈልበት የነዳጅ ማደያ እንዳለም ጠቁመዋል። አስተያየት ሰጭው አያይዘውም ነዳጅ ተቋማዊ ሆኖ ሊመራ ይገባዋል ብለዋል። የስብሰባ ተሣታፊ የሆኑት ኮሚሽነር አበበ ውቤ ከዚህ ውይይት የተረዳነው እኛ የፀጥታ መዋቅር የሌባው ተባባሪ እንደሆነን ነው የተሠማኝ ብለዋል። በመካከላችንም ተላላኪ ደላላ አለ ጉራማይሌ አመራርም በትልቁ ተፈጥሯል ። ውስጣችን መፈተሽ አለብን የሚመታ ካለም መመታት አለበት ያሉ ሲሆን የንግድ ቢሮ ሳያውቀው የሚወጣ ነዳጅ መኖር የለበትም ፤ ንግድም በስሩ ያሉት ተባባሬና የጥቅሙ ተጋሬ ላይ ርምጃ መውሰድ አለበት ነው ያሉት። የክልልሉ የፍትህ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አያሌው አባተ (ዶ/ር) ችግሮች የሚመነጬት ያሉ እውነታዎችን ፊት ለፊት አውጥቶ ካለመነጋገር ነውና ችግሮች ፍንትው ብለው ወጥተው በቅንጅታዊ አሰራር ፈጥነን ልንፈታቸው ይገባል ያሉ ሲሆን ጉዳዩ የሚመለከተው ተቋምም ከዚህ ተመልሶ ራሱን እንደገና ማየት እንዳለበት አሳስበዋል ።...
- 1
- 2
