













የገበያ ማዕከላት መስፋፋት የዋጋ ንረትን ለመቀነስና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት ወሳኝ መፍትሔ ሆነዋል-ሸማቾች
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሀይቅ ከተማ የመስክና የቢሮ ስራዎችን ምልከታ አደረገ።
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሀይቅ ከተማ የመስክና የቢሮ ስራዎችን ምልከታ አደረገ።
"ህጋዊ፣ ተደራሽና ዘመናዊ የንግድና የግብይት ስርዓት እንገነባለን" በሚል መሪ መልዕክት፣ የንግድ ቀን በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በጫጫ ክፍለ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት በድምቀት ተከብሯል።
photo_2026-06-17_09-59-39 (6)
photo_2026-06-17_09-59-39
photo_2026-06-17_09-59-40 (2)
photo_2026-06-17_09-59-40 (3)
photo_2026-06-17_09-59-40 (4)
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሀይቅ ከተማ የመስክና የቢሮ ስራዎችን ምልከታ አደረገ።
photo_2026-06-17_09-59-40 (6)
photo_2026-06-17_09-59-40 (7)
photo_2026-06-17_09-59-40 (8)
photo_2026-06-17_09-59-40














የቢሮ ኃላፊ መልዕክት

ኢብራሒም ሙሀመድ (ዶ.ር)
የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ
የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2022 ዓ.ም በህግና በገበያ ስርዓት የሚመራ ዘመናዊና ተወዳዳሪ የንግድና ግብይት ስርዓት ተፈጥሮ ማየት የሚል ራዕይ ነድፎ ራዕዩን ለማሳካት ሌት ተቀን እየሰራ ያለ ተቋም ነዉ፡፡ ተቋሙ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪ፣ ፍትሀዊና ተደራሽ የንግድና ግብይት ስርዓት ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል። የንግድ ስርአቱን የሚያዛቡ አሻጥሮችን፣ የደላላ ጣልቃ ገብነትን፣ የገበያ ተደራሽነት ችግሮችን፣ ህገወጥ የኬላ ቀረጦችን እና የምርትጥራት ችግሮችን ለመፍታትዘርፈ ብዙ ተግባራትን ከማከናወንም በላይ ንግድ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የታገዘ እንዲሆን አዳዲስ ሲስተሞችን የማስለማትና ሌሎች ንግድና ግብይቱን ወደ ህጋዊ አሰራራ የሚያመጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ለህጋዊ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና በህገ ወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው በተገኙ ህገ-ወጦች ላይ ደግሞአስተዳደራዊና ህጋዊ ርምጃ በመዉሰድ የሸማቹን ደህንነት ለማስጠበቅ ጥረት ተደርጓል።
News | ዜናዎች
June 8, 2026
Comment (0)
በወቅታዊ የነዳጅ ስርጭት ችግሮች ዙሪያ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከሚመለከታቸወ አካላት በተገኙበት ውይይት አካሒዳል። ለመወያያ መነሻ የሚሆን ጽሁፍ በንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ በአቶ ፈንታው ፈጠነ ቀርቧል። በነዳጅ አጠቃቀም ዙሪያ የወጡ አዋጆችን ፣ በአዋጁ መሰረት የተሰሩ ስራዎችን፣ በአሰራር ላይ የመስተዋሉ ተግዳሮቶችንና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በዝርዝር ለታዳሚያን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ፈንታው ፈጠነ አቅርበዋል ። በፀጥታና በፈፃሚ ስም እየገቡ የነዳጅ ስርጭት ሂደቱን የሚያውኩ አካላት እንዳሉም አቶ ፈንታው ሳይጠቁሙ አላለፋም። ተሳታፊ አካላት በአሰራሩ ላይ እያጋጠሙ የሉ ችግሮችንና መፍትሔዎችን በዝርዝር አንስተዋል። ከተሰጡ አስተያየቶ አንድ የፖሊስ አመራር እንደገለፁት ነዳጅ ማደያ ተቋማዊ ሳይሆን ግለሰባዊ ነው ። አስተያየት ሰጭው ነዳጅ ማደያ ላይ ደላላው ፣ ማደያውና አንድ ሌላ ተጠቃሚ አለ ያሉ ሲሆን ለወረፋ አስከባሪ በቀን 5000 ብር የሚከፈልበት የነዳጅ ማደያ እንዳለም ጠቁመዋል። አስተያየት ሰጭው አያይዘውም ነዳጅ ተቋማዊ ሆኖ ሊመራ ይገባዋል ብለዋል። የስብሰባ ተሣታፊ የሆኑት ኮሚሽነር አበበ ውቤ ከዚህ ውይይት የተረዳነው እኛ የፀጥታ መዋቅር የሌባው ተባባሪ እንደሆነን ነው የተሠማኝ ብለዋል። በመካከላችንም ተላላኪ ደላላ አለ ጉራማይሌ አመራርም በትልቁ ተፈጥሯል ። ውስጣችን መፈተሽ አለብን የሚመታ ካለም መመታት አለበት ያሉ ሲሆን የንግድ ቢሮ ሳያውቀው የሚወጣ ነዳጅ መኖር የለበትም ፤ ንግድም በስሩ ያሉት ተባባሬና የጥቅሙ ተጋሬ ላይ ርምጃ መውሰድ አለበት ነው ያሉት። የክልልሉ የፍትህ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አያሌው አባተ (ዶ/ር) ችግሮች የሚመነጬት ያሉ እውነታዎችን ፊት ለፊት አውጥቶ ካለመነጋገር ነውና ችግሮች ፍንትው ብለው ወጥተው በቅንጅታዊ አሰራር ፈጥነን ልንፈታቸው ይገባል ያሉ ሲሆን ጉዳዩ የሚመለከተው ተቋምም ከዚህ ተመልሶ ራሱን እንደገና ማየት እንዳለበት አሳስበዋል ።...
June 8, 2026
Comment (0)
መድረክ ተካሄደ፡፡ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከግብርና ምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር በተመረጡ ዞኖች ለሚገኙ የግብርና ምርቶች ግብይት ቡድን፣ ለግብርናው ሴክተር አካላትና አንዲሁም የንግድና ገበያ ልማት ሴክተር አካላት፣ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ም/ ኃላፊና ቡድን መሪዎች በተገኙበት በምርት ትስስር ርዕሰ ጉዳይ ላይ .የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሂዷል ፡፡ በንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሰብል ግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ልንገረው ሀበሻ ለገበያ ትስስር የተዘጋጀውን መዋቅራዊ ሰነድና የአርሶ አደር የግብይት ቡድን አደረጃጀት የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በዝርዝር ለተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን የተነሱ የተሳታፊ ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ ማብራሪያ ሰጥጠዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ችግሮችን ለመፍታት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸው ሁሉም አካል በአሰራሩ መሰረት ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እየፈታ ሊሄድ ይበገባዋል ብለዋል፡፡ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ይህን ጠቃሚና ሳይንሳዊ የግብይት ትስስር እውን ማድረግ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ቢታወቅም በተግባር ወደስራ ሲገባ በርካታ ችግሮች ስላሉ ተባብረን ልንፈታቸው ይገባል ብለዋል፡፡ እንደችግር ከተነሱት መካከል ፡- ነጋዴዎች ተመሳጥረው ዋጋ ይወስናሉ፣ የዳላላ ጣልቃ ገብነት አሁንም አልቀረም፣ የግብይት ቡድኑ በትክክል ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም እንዲያውም ለአምራቹ ከመቆም ይልቅ ከደላላ ጋር ይመሳጠራል፣ ነዳጅ ስንጠይቅ ማደያዎች ያንከላክሉናል የሚሉና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ግብይት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አትክልት አሳቤ የግብርና ምርት ትስስር የአምራቹንና የሸማቹን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ፣ አምራቾች ሳይዋከቡ ምርታቸውን እንዲሸጡ የሚያደርግ፣ ሸማቾች የተሻለ የገበያ አማራጭ እንዲኖራቸው የሚያደርግ፣ በትክክል ተግባራዊ ከተደረገም የደላላ ጣልቃ ገብነትንና የህገ ወጥ ነጋዴዎችን አሻጥር የምንበጥስበት፣ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት አውን ካደረግነው ምርታማነትን የሚሳድግ የክልሉን የኢኮኖሚ ገጽታ መቀየር የሚያስችል አሰራር በመሆኑ ይህን ተግባር በጥብቅ ዲሲፕሊን ይዞ መስራት ሁሉንም አካል ተጠቀሚ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡ ወይዘሮ አትክልት ዐያይዘውም ይህ የገበያ ትስስር የተለያዩ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር የሚጠይቅ በመሆኑ በመካከላችን ምንም ዓይነት መገፋፋት ሳኖር በፍጹም የሃላፊነትና የትብብር መንፈስ መስራት ይገባል፤ ለዚህ ደግሞ አሁን ያለውን የገበያ መሰረተ ልማት ማስፋፋት ቁርጠኝነት እንደ ምቹ አጋጣሚ መውሰድ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ለተነሱ ጥያቄዎችም ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡...
June 8, 2026
Comment (0)
የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ፡፡ “ብሔራዊ ጥቅምና ጂኦ- ስትራቴጂ ቁመና” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ በተዘጋጀ ሰነድ የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት አካሂደዋል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የማንሰራራት ላይ የምትገኝ ለቀጠናው ሰላም እና እድገት ጉልህ ድርሻ ያላት የታላቅ ህዝቦች መኖሪያ ናት ሲሉ የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፈንታው ፈጠነ መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ሲከፍቱ ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያን የመለወጥ ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው፡፡ ሁሉም ይመለከተዋል፡፡ ሀገሪቱ እያደረገች ያለውን የመለውጥና ብልፅጋናን የማረጋገጥ ተግባር በባለቤትነት መደገፍ ይገባል ሲሉ ምክትል ኃላፊው አሳስበዋል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና(ራስነን መቻል፣ከድህነት መውጣት፣መበልጸግ) ፣ ሀገራዊ ህልውና እና ደህንነት ማስፈን፣ ፖለቲካዊ አቅምንና ተጽዕኖ ፈጣሪነትን ማሳደግ፣ የባህል ነፃነትናተፅኖ ፈጣሪነት ማጉላት፣የህዝቦች ማህበራዊ ልማት(ትምህርት፣ጤና፣ማህበራዊ ዋስትና). የመሳሰሉ የብሔራዊ ጥቅም መሰረታዊ ግቦቻችን መሳካት ሁሉም የየድራሻውን መወጣት ይኖርበታል ሲሉ የመወያያ ፅሁፉን ያቀረቡት የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አማካሪ ሙሀመድ ጀማል(ዶ/ር) አስገንዝበዋል፡፡...
